የማይደክመው የአቅቤ- እምነት ሰው
ዶ/ር ነቢል ቁረሺ
1983 – 2017 ዓ.ም
የማይደክመው የአቅቤ- እምነት ሰው
ታሪክ የማይረሳቸው ታሪከኞችን ስናስታውስ ነቢሊ ቁረሺን የመሰለ የወንጌል ጀግኖናን መርሳት ከባድ ነው፡፡ ሴፕቴምበር 16- 2017 አምላክ ልጁን የጠራበት ቀን ነበረች የህመሙን ዜና ከሰማሁባት ቀን ጀምሮ በብዙ አዝኜ ነበር፡፡ በሞቱ ወዳምላኩ እንዲሄድ ባውቅም በህይወቴ ላገኛቸው ከምመኛቸው ሰዎች ውስጥ ስለነበር ነው፡፡
የህይወት ምስክርነታቸውን ደጋግሜ ብሰማም ሁሌም ከምደነቅባቸው ሰዎች ውስጥ ነቢል ቁረሽ አንዱና ዋናው ነው፡፡ ዛሬ "ሲኪንግ አላህ ፋይንዲንግ ጂሰስ" ወይም "አላህን ስፈልግ እየሱስን አገኘውት" የሚለውን መጸሐፉን ሳነብ ይበልጥ የዚህ የወንጌል ጀግና ማለፍ ተሰማኝ፤ አንድንም ነገር አሰብኩ ማን ነው ተረኛው ነቢል ቁረሺ? እውነትን ፈልጎ ያገኘ፣ ይህን እውነት ደግሞ ለጨለማው ዓለም ለማድረስ የሚተጋ ማን ይሁን ተረኛው ነቢል ቁረሺ? ማነው ተረኛው በዚህ የወንጌል አርበኛ አገልግሎት ብዙ ሺዎች በተለይ በእስልምና አለም ውስጥ ያሉ ሰዎች እውነት በርቶላቸውል፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች የሆነውን ድህነት ተቀብለዋል፡፡
መልካም ንባብ!
ነቢል ቁረሺ ካሊፎርኒያ ግዛት ሳንዲያጎ ከተማ በ1983ዓ.ም ከፓኪስታን ወደ አሜሪካ በገቡ ስደተኛ ቤተሰቦቹ ተወለደ፡፡ ከአባቱ የባህር ሃይል ሰራተኛነት የተነሳ ቨርጂኒያ ግዛት እስካረፉበት ግዜ ድረስ በልጅነቱ ብዙ ቦታዎችን እየተዟዟሩ ኖረዋል፡፡ ጥብቅ በሆነ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ቤተሰብ ውስጥ ተወልጆ እንዳደገ ይናገራል ለዚህ ደግሞ አያቱ እና ቅድመ አያቱ ምዕራብ አፍሪካ እና ኤንዶኔዢያ የኢስላም ሚሲዬናውያን ሆነው እስልምናን ካስፋፉ አንቱ ከተባሉ ሰዎች አንዱ መሆናቸው እንደ ምክኒያት ይነሳል፡፡ ቤተሰቡም አሜሪካ ለረጀም አመታት ይኑሩ እንጂ የምዕራባውያንን ባህል ላለመጋራት ጥብቅ በሆነ ኢስላማዊ ስርዓት እና ትምህርት ኖረዋል፡፡ ነቢልም በአስተዳደጉ እነዚህን ስርዓቶችን እና አስተምሮዎችን መጠበቅ ከሁሉ በላይ እንደሆነ እየተነገረው እና እየተገበረው ኖሯል በአንድ ፕሮግራም ላይ ነቢል ስለአስተዳደጉ ሲያወራ እንዲህ ይላል እናቴ ሁሌም እንዲህ ትለኛለች ነቢል በምትሄድበት ቦታዎች ሁሉ በትምህርት ቤት፣ መንገድ ላይ ሰዎች ገና ፊትህን እንዳዩህ እንዲም ይላሉ እርሱ ሙስሊም ነው፤ ስለሆነም አንተ የእስልምና አምባሳደር ነህ ስለዚህም እስልምናን በሚገባ ልትወክል እና ልታሳይ ይገባሃል፣ በትምህርት ቤትህ በጣም ሰው አክባሪ መሆንህን እርግጠኛ ሁን አስተማሪዎች ከክፍላችሁ ካሉ ተማሪዎች በላይ አክባሪ እና ስነስርዓት ያለህ ተማሪ መሆንህን ማየት አለባቸው ምክኒያቱም አንተን በሚያዩበት መንገድ ነው እስልምና ማለት ይህ ነው ብለው የሚተረጉሙት፣ የማትዋሽ እና በስብዕናህ የላቅ ልጅ መሆንህ አሳይ ትለኛች ፡፡
ከዚህ ባለፈ ቤተሰቦቼ በጣም ጥሩ እና መልካም የሆነ ሙስሊም እንድሆን አስተማሩኝ ይህም ማለት ደግሞ የእስልምናን አስተምሮዎች መከተል ነው፡፡ ይህ እንዴት መሰላችሁ ለምሳሌ ስምንተኛ ክፍለ ሆኜ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ እግሬ ከአልጋው ወርዶ መሬት ሳይነካ እናቴ ያስለመደችኝ ጸሎት አለ ፣ ከዛም ወርጄ ወደ መጸዳጃ ቤት ከመግባቴ በፊት ግራ እግሬ ቀድሞ መግባቱን አረጋግጣለሁ ይህ ምን ያህል ቤተሰቤ የእስልምናን ስርዓቶች አጥባቂ እንደነበር ያሳይል፡፡ በታሪክ ነቢዩ መሀመድ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ ግራ እግሩን አስቀድሞ እንደነበር ይነገራል መሀመድ ይህን ካደረገ እርሱ የፈጣሪ መልዕክተኛ ነውና እኛም እናደርገዋለን፤ ይህ የመሰጠታችን ልክ ነበር፣ መጸዳጃ ቤት ከገባሁም በኃላ "ዋዱ" የተሰኘውን የመታጠብ ስርአት ፈጽማለሁ በዚህም በቀን ውስጥ ካሉ አምስጥ ጸሎቶች ለአንደኛው እራሳችሁን ታዘጋጃላችሁ፣ ለመጸለይም ምንጣፌን እያዘጋጀው ከጸሎቱ በፊት የምፀልያቸው ጸሎቶች አሉ እነርሱንም ስጨርስ ነው የቀኑን የመጀመሪያ ጸሎት ምጸልየው ይህ ሁሉ ደግሞ በአረብኛ ነው፤ ጸሎቶቹም ሁሉ እኔ ከልቤ ምጸልያቸው ሳይሆኑ የሸመደድኳቸው ናቸው፣ ከዛም ለቁርስ እቀርባለው ከመብላቴ በፊት እጸልያለው ከዛም እናቴ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ስወጣ ትከተለኝና ሙሴ ለፈንኦን ከመናገሩ በፊት እግዚአብሔር ድፍረት እና ጥበብ እንዲሰጠው የጸለየውን ጸሎት መጸለይ አትርሳ ትለኛለች ይህንንም ወደ ትምህርት ቤት እየሄድኩ ዘውትር እጸልያለው፡፡ ይህ የእያንዳንዱ ቀን ተግባሬ ነበር ይህ ብቻ ሳይሆን የቁርአኑን የመጨረሻ ሰባት ምዕራፎች በአምስት አመቴ በቃሌ መናገር እችል ነበር ምክኒያቱ ደግሞ በቀን ውስጥ ባሉ አምስት ጸሎች የምንጸልያቸው ስለነበሩ ነው፣ በ15 ዓመቴ ደግሞ የቁርአኑን የመጨረሻ 15 ምእራፎችን በቃሌ ይዤ ነበር ፣ ሙሉ ቁርዓንን ደግሞ በአረብኛ በአምስት አመቴ አንብቤአለሁ ይህ ምን ያህል ጠንካራ ሙስሊም ቤተሰብ እና የኃላ ታሪክ እንዳለኝ እንድታዩ ነው ፡፡
ይህ ግን ሌላ ተቃራኒ ጎን ነበረው እናቴ ሁሌም አንተ የኢስላም አንባሳደር ነህ ስትለኝ ወደ ትምህርት ቤት ሄጄ ሌሎችን ስለእስልምና እንዳስተምር፣ እንድሞግት እና ወደ እምነቱ እንድጋብዝ ነበር፡፡ ስለዚህም ወንጌል አማኞች ስለ ክርስቶስ ወንጌል ሊነግሩኝ በሚሞክሩ ግዜ እኔ የተዘጋጁ ጥቅሶች እና መልሶች ነበሩኝ ፡፡ አስታውሳለሁ አስራ አንደኛ ክፍል ሁኜ አንዲት ቤትሲ የተባለች የክፍል አጋሬ ስለ ክርስቶስ ልትነግረኝ ሞከረች እንዲህም ጠየቀችኝ ኢየሱስን ታውቀዋለህ ብላ እኔ ግን ተዘጋጅቼ ነበርና አዎ አውቀዋለው አልኳት በቁርዓናችን መሰረት ኢየሱስ ከድንግል እንደተወለደ፣ ብዙ ድንቅ ተዓምራትን እዳደረገ፣ እንደፈወሰ፣ ሙታን እንዳስነሳ፣ በዘመን ፍጻሜም ደግሞ ተመልሶ እንደሚማጣ አምናለው አልኳት በድንጋጤ ትመለከተኝ ጀመር ሙስሊሞች ይህን እንደምናም እውቀቱም አልነበራትምና እኔም ይህን ተጠቅሜ ኢየሱስ ግን አምላክ አይደለም አልኳት ይህ ለሙስሊሞች ትልቅ ሃጢያት እና ክህደት ነውና፤ እርሷም አይደለም ነቢል ብላ ልታስረዳኝ ሞከረች እኔም እስኪ ኢየሱስ የቱ ጋር ነው አምላክ ነኝ ያለው ብዬ ጠየኳት ልታስረዳኝ ሞከረች ግን መልሷን አጣጣልኩት እርሷም ዝምታ ወረሳት እኔም ቀጥዬ ቤትሲ ስለክርስቶስ ማወቅ ከፈለግሽ ስለ እስልምና ጠይቂኝና አስተምርሻለው አልኳት ለዚህች ልጅ ያለኝ አክብሮት ግን እጅክ ከፍ አለ ፤ ለረጅም አመት ክርስቲያን ጓደኞቼ ስለክርስቶስ ነግረውኝ አያውቁም ጥያቄም ይፈጥርብኝ ነበር ቆይ ስለዕምነታቸው ግድ አይላቸውም እንዴ ሚል ጥያቄ ይፈጠርብኝ ነበር፡፡
ታዲያ በእንደዚህ ጥብቅ የእስልምና አስተምሮ እና ልምምድ ያደግገው ነቢል ቁረሽ እንዴት ለኢየሱስ እጁን ሊሰጥ ቻለ፡፡ ለዘመናት እውነት ብሎ የተከተለው እና ለብዙዎች ያጋራውን እስልምና ትቶ ሌላ የሚበልጥ መልዕክት የተሻለ እውነት መዳኛ መንገድ አለ ብሎ ሊያስተምር ሆነ ፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሆኖ ከብዙ ክርስቲያኖች ጋር ስለ መዳኛ መንገድ ያወራ ነበር ከብዙ የተለያዩ እምነት ተከታዬች ጋር ግዜ ያሳለፍ ነበር ካገኛቸው ሰዎች ሁሉ ውስጥ ግን ከአንድ ልጅ ጋር ጥሩ ቀረቤታ መሰረተ ዴቪድ ይባላል ይህም የሆነው ዴቪድም እንደርሱው ለእምነቱ ትልቅ ቦታ ይሰጥ ስለነበር ነው፡፡ ነገሮችን ሁሉ የቀየረች አጋጣሚም ልዩ ነበረች ፡፡
ይህ ጽሑፍ ከተልዕኮአችን ቅጽ አንድ ላይ ከተሰራው ላይ የተወሰደ ነው፡፡ የዚህን ታሪክ ሙሉ ጽሑፍ በፒዲ ኤፍ ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኙታል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ያንብቡ፡፡
ቴሌግራም፡- https://t.me/Mission_Mobilization_Ethiopia