ያልተደረሱ ቡዲስቶች
በቲቤት፣ታይላንድ፣ቬትናም፣ሴሪላንካና በሌሎች ብዙ ቡዲስት ሀገራት ቡርትካናማ የለበሱ መነኮሳት በእያንዳንዱ ጠዋት ቤት ለቤት እየዞሩ ምግብ ይሠበስባሉ። ስለተሠጣቸውም ምስጋናን አያቀርቡም ምክንያቱም ከሞት በኃላ ሌላ ስጋን ለብሶ በመነሳት እምነት የተሻለ ደረጃን እንዲያገኙ ዉለታን እየዋሉላቸው እንደሆነ ስለሚያስቡ።
ቡዲዝም በሲደርታ ጋውሌማ የስድስተኛ መቶ አመት (አመተ ዓለም) አስተምህሮ ላይ የተመሰረተ ነው። ወደ በኃላ ሲደርታ ቡድሃ በመባል መጠራት ጀመረ።
ህይወት የህመም ንድፍና በምኞት ምክንያት የሚመጣ ጭንቅ ውጤት እንደሆነች አስተምሯል።
የሰውን ምኞት መግታት ፣ለጭንቅ ፍፃሜ ምልክት ነው። የህይወት ግብ ምኞትን በማስቀረት በፍጥነት
መራመድ ነዉ። ይሄም ነርቫና በመባል ይታወቃል።
በሶስተኛ መቶ አመት (አመተ ዓለም) በአሁን በሴሪላንካ ደሴት ላይ ፣የቡዲስት አስተምህሮ በፖሊ ቋንቋ (ከሳን ስክሪፕት ጋር የተያያዘ ) በፅሁፍ ተጠናቆ ነበር፤
ሀይማኖታዊ ያልሆነ ፣ፍልስፍናዊ የቡድሂዝም ጎኖች፦ከአምላክ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም። ይህ ግልጽ የሆነ ህግ ነው። አስተምሮቱ ነፍስ እንደሌለ ይገልጻል። የማንነት ማዕከል የለም። ባይሆን ሰው የአምስት "ካህንዳዎች ድምር ነው። እነዚህም የማንነት ምስያ ይሰጣሉ። ይህም የማንነት ምስያ ጭንቀት፣
ውጥረትና ምኞት በስነስርዓቱ ሲወገዱ ይጠረጋል። ስነስርዓት እየዋለ እያደረ ሀርነርቫና ይወስዳል (ባዶነትና ራቁትነት)ምኞትን የማጣት ደረጃ ፍፁም ሰላምንና ፍፁምነትን ያስገኛል። የቡዲዝም ታዋቂ ልምምድ አብዛኛውን ጊዜ ሽልማት የሚያስገኙ ስራዎችን መስራትና ክብረ በአላትን ድግሶችን ያካትታል ።
በቡድሂስት ሀገራት ዜጎች የመነኮሳት ዜማ "ሲትራ"፣ የተጠበቀ የምርቃት ደንብ፣ በቤት ክብረ በዓላት ላይ ፣በቀብር እና የመታሰቢያ ስርዓት ላይ ለሟች ጥቅም ሬሳ የማቃጠል ተግባር ያከናውናሉ።
ቡድሂዝም አስተምህሮ ለተከታዮቹ ስምንት እጥፍ ክብር ሚያመጡ፤ ከአምስት የአታድርጉ ህግጋት ጋር ያስቀምጣል እነሱም አትስረቅ፣ አትዋሽ ፣ አታመንዝር ፣አትጠጣ (አትስከር) የሚሉ ናቸው። አብዛኛው የቡድሂዝም እምነት ተከታዮች ግዴታዎቻቸውን ለመቀነስና ሽልማት ለማግኘት ቀላል መንገዶችን ይከተላሉ። ካርማ በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ የመጥፎና መልካም ተግባሮች ድምር ነው።ቡድሂዝም በብዙሃኑ እንደሚደረገው ሽልማት ለሚያስገኙ መነኮሳት መልካም ተግባርን ማድረግ ፣ በክብረ በዓላትና መንፈሳዊ ስርዓቶች ላይ መሳተፍ ፣ለቡድሂስት ቤተ መቅደስ እድሳትና ግንባታ መዋጮ ማድረግ መሠረታዊ ነገር ነው።
ዛሬ በዓለማችን ከአምስት መቶ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህን እምነት ይከተላሉ፡፡ እንደወንጌል አማኝ አንድ ነገር ይገባናል እየሱስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገር የእግዚአብሔር አስደናቂው ፈፍቅር አንድያ ልጁን በመስጠት የተገለጠ ነው፤ በዚህ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ እንድናምን ግን የእኛ ውሳኔ ነው፡፡ ዛሬ አንድ ደቂቃ በዚህ እምነት ውስጥ ለሚገኙ እውነት እና ህይወትን ረብ የለሽ በሆኑ ውጣ ውረዶች እየፈለጉ ላሉ ህዝቦች ለመጸለይ እውሰድ፡፡
ምንም እንኳ ቡድሂዝም ሰዎች በአለመቻል (በሳምሳራ) ተይዘው እንዳሉ ቢያስተምርም፣ የሰው ውልደት እና ሞት የዘለአለም ኡደት ፣ላልተወሰነ ጊዜ ቀጣይነት ያለው የሰው እጣ ፈንታ በዳግም ውልደት በሚሸጋገሩበት ሂደት ሚወሰን እንደሆነ ያስረዳል፤ ነገርግን ጥቂት አይነተኛ ቡድሂስቶች ወደፊት የሚፈጥሩበትን ደረጃ ወይም ናንቫናን የማግኘት ኡደት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ምክንያቱም ህይወታቸው ለመኖር በሚደረግ ትግል የተሞላ ነዉ።ሽልማትን የማግኘት ፍላጎታቸው የአሁኑን ህይወት ከማሻሻል ጋር የተያያዘ ነው። ብዙ የቡድሂዝም ተፋላሚዎች ከዘላለም የካርማ ህግ ማንም ሊከልላቸው እንደማይችል ያምናሉ። ምክንያቱም ያለፈው የህይወት ሁነት የአንድን ሠው የጭንቅ ደረጃ ይፅፋል። በ40ቀን እድል ማመናቸው ብዙዎችን በብዙ መናፍስት መኖር እያመኑም ቢሆን የቡድሂዝም እምነት እንዲከተሉ ያደርጋቸዋል። ከቡድሂዝም ፍልስፍና ስር ማለትም አምላክ አለመኖሩንና የሠው ነፍስ አለመኖሩን ቢያስተምርም ብዙ ቡዲህስቶች ግን የጥንት የመናፍስት እምነቶቻቸውን ደብቀው በፍርሃት ይኖራሉ።
ዛሬ በዓለማችን ከአምስት መቶ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህን እምነት ይከተላሉ፡፡ እንደወንጌል አማኝ አንድ ነገር ይገባናል እየሱስ ያስፈልጋቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገር የእግዚአብሔር አስደናቂው ፈፍቅር አንድያ ልጁን በመስጠት የተገለጠ ነው፤ በዚህ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ እንድናምን ግን የእኛ ውሳኔ ነው፡፡ ዛሬ አንድ ደቂቃ በዚህ እምነት ውስጥ ለሚገኙ እውነት እና ህይወትን ረብ የለሽ በሆኑ ውጣ ውረዶች እየፈለጉ ላሉ ህዝቦች ለመጸለይ እውሰድ፡፡
ትርጉም ፡- ምህረት በቀለ
ምንጭ ፡- Wikipedia.com, Joshua.org