ሚሽን ሞብላይዤሽን ኢትዮጵያ
Mobilize - Develop - Accelerate
የአገልግሎታችን የትኩረት አቅጣጫዎች
በዚህ አገልግሎት ውስጥ አራት መሰረታዊ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን እነርሱም አጥቢያ ቤተክርስቲያኖችን ለታላቁ ተልዕኮ ንቁ፣ ብቁ እና ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ማስተማር፣ ማስተማበር እና ማሰማራት፣ የተልዕኮን ስራ የሚያንቀሳቅሱ የጸሎት ንቅናቄዎች ይፈጠሩ እና ይበረቱ ዘንድ መስራት፣ የዲጅታል ሚዲያ ምህዳር ላይ አማኞችን በተልዕኮ ማስተማበር መድረስ፣ የተልዕኮ ጥናት እና ምርምር ላይ መስራት ናቸው፡፡
ትምህርት እና ስልጠናዎች
ታላቁ ተልዕኮ ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ የቤት ስራ ነው፡፡ አማኞች የተሰጣቸውን የቤት ስራ የሚወጡ ብቁ ሰራተኞች ይሆኑ ዘንድ ማወቅ መረዳት እና መሰማራት ይኖርባቸዋል ስለሆነም ከአጥቢያ ቤተክርስቲያኖች ጋር አጋር በመሆን እና በመደገፍ የተልዕኮ ትምህርት እና ስልጠናዎችን በመስጠት የተዘጋጁ ሰራተኞችን እና የወንጌሉ ተሳታፊዎችን ማፍራት ትኩረታችን ነው፡፡
የጸሎት ንቅናቄዎችን
ያለ ጸሎት መንፈሳዊ ዓለም ላይ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ የወንጌል ተልዕኮ ንቅናቄ ከምድራችን እንዲነሳ የጸሎት ሃይል መብዛት አለበት፡፡ ሚጸልይ ሰው የወንጌል ልብ ይካፈላል፣ ሚጸልይ ቤተሰብ የወንጌል አቅም ይሆናል፣ የሚጸልይ ቤተክርስቲያን ሚሲዮናዊያንን የሚልክ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በቤተክርስቲያኖች በተለያዩ ስፍራዎች ተልዕኮ ተኮር የሆኑ የወንጌልን ስራ ይዘው ሚማልዱ፣ ሚዋጉ የጸሎት ቡድኖች እንዲበዙ እንሰራለን፡፡
ዲጅታል ሚሽን ሞብላይዤሽን
ዛሬ የዓለማችን 62% ሚሆነው ዜጋ ንቁ ኢንተርኔት ተጠቃሚ እንደሆነ ጥናት ያሳያል በቁጥር ሲገለጽ ይህ ማለት 4.9 ቢሊዮን የሚጠጋ የዓለም ህዝብ ኢንተርኔት ይጠቀማለን፡፡ የዲጅታል ሚዲያ ምህዳሮች ያላመኑ ሰዎችን በወንጌል ለመድረስ አይነተኛ ስፍራዎች ናቸው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ግን የወንጌል አማኙን ማህበረሰብ ለወንጌል ተልዕኮ ለማስታጠቅ ትልቅ መስክ የሚሆን ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ፕሮግራም የዲጅታል ስነ-ጽሑፍ ስራ፣ የማህበራዊ ድህረ ገጾች እና የኦዲዮ ቪዡዋል መስክ ላይ በመስራት አማኞችን የመስታጠቅ ስራዎችን እንሰራለን፡፡
የተልዕኮ ጥናት እና ምርምሮች
የወንጌል ተልዕኮ አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን ከሚያስፈልጉን መሰረታዊያን አንዱ የተልዕኮ ጥናት እና ምርምር አገልግሎት አንዱ ነው፡፡ በወንጌል ስላልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎች፣ ስለወንጌል ስራ እድሎች እና ተግዳሮቶች፣ ስልቶች እና መርሆች ላይ በጥልቀጥ የሚሰሩ የተለያዩ ጥናቶች እና ምርምሮች ላይ መስራት አስፈላጊ ነው፡፡
የወንጌል ጥናት እና ምርምር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን የወደፊቱን አቅጣጫ ለመጠቆም፣ መስመር ለማስያዝ እና የወንጌል ተልዕኮ ስራን ለመደገፍ መሰረታዊ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በምድራችን ኢትዮጵያ ያለውን የወንጌል አገልግሎት የሚደግፍ የተለያዩ ጥልቀት እና ትኩረት ያላቸው ጥናቶቸ እና ምርምሮች ላይ እንሰራለን፡፡